የመንገድ ትራንስፖርት ኣገልግሎና የመናሃርያ ኣስተዳደር የሥራ ሂደት

Print

ራዕይ

ድሕንነቱ የተጠበቀ ዘመናዊ የትራንስፖርት ኣገልግሎት ተደራሽ ሆና ማየት።

ተልዕኮ

ፈፃሚ ኣካላትን በብቃት በመምራት፣ በማስተባበር፣ ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ እንዲሁም የግል ባለሃብቶች ተሳትፎ በማሳደግ አስተማማኝ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስፋፋ በማድረግ የክልላችን ልማት ጉልህ ሚና እንዲጫወት ማድረግ።

የሥራ ሂደቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል

1.  ቀልጣፋ፣ብቁ፣ኢኮኖሚያዊ እና የተመጣጠነ የትራንስፖርት ሲስተም እንዲስፋፋ ማድረግ፣

2.  የትራንስፖርት ኣገልግሎት ድህንነቱ የተጠበቀና ምቾት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣

3.  ክልላዊ የትራንስፖርት አገልግሎት መስመሮች እንዲዘረጉና እንዲደራጁ ማድረግ፣

4.  ትራንስፖርት በማንኛውም ረገድ እንዲያድግ ማበረታታት፣

የመንገድ ትራንስፖርት ኣገልግሎና የመናሃርያ ኣስተዳደር የሥራ ሂደት ተግባሮች

 

1.  ደህንነቱ የተረጋገጠ፣ቀልጣፋ የተሟላና የተመጣጠነ የትራንስፖርት አገልግሎት መኖሩን መከታተል፣

2.  በክልል ደረጃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስመሮች እንዲዘረጉ ማድረግ፣

3.  መንገደኞች፣ዕቃዎችና ፖስታዎች በንግድ ትራንስፖርት ስለሚጓዙበት ሁኔታ መመሪያ ማውጣትና ኣፈፃፀሙ መከታተል፣

 

 

Copyright©2012 Tigray Bureau of Construction, Road and Transport. All rights reserved.